ተጨማሪ ክፍያን ከሰራተኞች ደሞዝ የመቁረጥ አካሄድ በድጋሜ እንዲታይለት ኢሰማኮ ጠየቀ

ኑሮአቸው ከእጅ ወደ አፍ የሆኑ ሰራተኞች አሁን እየተከፈላቸው ባለዉ ዝቅተኛ ደሞዝ የኑሮ ዉድነቱን ጫና መቋቋም አቅቷቸዋል ተብሏል።

ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር ባልቻሉበት ሁኔታ ተጨማሪ ክፍያ ከሰራተኛው ደሞዝ መቁረጥ የበለጠ ኑሮዉን ስለሚያከብደዉ ሊታይ እንደሚገባ ተገልፆል።

የመንግሥትና የግል ሠራተኞች ከደመወዛቸው ላይ ተቆራጭ በማድረግ፤ ለአደጋ ስጋት የሚሆን ክፍያ እንዲፈፅሙ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ  ለምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  መመራቱ የሚታወስ ነዉ።

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን መንግስት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ሲል ጠይቋል።

ኮንፌዴሬሽኑ በኢትዮጵያ ለ50 ጊዜ የሚከበረዉን የሰራተኞች ቀን ተንተርሶ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ነዉ ይህንን ያለዉ።

የሰራተኞች ዋና ዋና ችግሮች ዙሪያ መንግስት ምላሽ እንዲሰጠዉ በመጠየቅ ቀኑን እንደሚያከብር የኢሰማኮ ኘሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ተናግረዋል።

ስምንት ያህል የሰራተኞች መብት ዙሪያ ላይ ያሉ  ነጥቦችን በማንሳት መልስ እንዲሰጥባቸዉ  ሲል አስታዉቋል።

ኮንፌዴሬሽኑ የዘንድሮውን በአል በዋጋ ንረት እና ካለበት በማይነቃነቅ ደሞዝ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮ በልቶ ማደር እየቸገረዉን ያለዉን ሰራተኛ እዉነታን የሚያንፀባርቅ ነዉ ብሏል።

ከዛ ባለፈ ሀሙስ የሚከበረዉን የሰራተኞች ቀንን በተለያዩ የፓናል ዉይይቶች እንደሚደረጉበት ተገልፆል።

ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *