አምራች ኢንደስትሪዎች ባሉበት እርከን ዉጤታማ ሆነዉ እንዲሰሩ ግን እየተሞከረ ነዉ ተብሏል።
የኢትዮጵያ ኢንተርኘራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ በኢትዮጵያ የጥቃቅን አምራች ኢንዱስትሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ አነስተኛ የሚሸጋገሩ አይደሉም ብለዋል።
አቶ አብዱልፈታህ ዉጤታማ ሆነዉ ወደ አነስተኛ እርከን የሚሸጋገሩ ሲሆን ዉስኖቹ ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ ይሻገራሉ ሆኖም ከፍተኛ የአምራችነት እርከን ላይ የሚደርሱት ግን ከ 5 በመቶ አይበልጡም ሲሉ ነግረዉናል።
የፋይናንስ እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች ተሟልቶላቸዉ እንዲሸጋገሩ ለማድረግ በተሰራዉ ስራ ወደ ከፍተኛ ያደጉ ስለመኖራቸዉ ግን ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ኢንተርኘራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተሱ አቶ አብዱልፈታህ መካከለኛ እና አነስተኛ አምራቾች የፋይናንስ አቅርቦት ማነስ የመስራት ፍላጎት ያላቸዉን አምራቾች በበቂ ደረጃ ወደ ስራዉ እንዳልገቡ ተናግረዋል ።
የመስሪያ ቦታ አቅርቦት ሌላኛ ችግር እንደሆነ የተቀመጠ ሲሆን ይህንን በክላስተር እና በግል ዘርፉን እንዲለማ ለማድረግ ስራዎች እንዳሉ ተቋሙ ጠቁሟል።
ተቋሙ በየደረጃዉ ያሉ የአስፈጻሚ አካላት የማስፈፀም አቅም ችግር እንደሆነበት ገልፆል።
በአስፈፃሚ አካላት ለማሳያም የአቅም ግንባታ ÷ የፋይናንስ እንዲሁም የመሬት ጥያቄዎች የሚመልሱ የአስፈጻሚ አካላት አለመናበብ እና መቀናጀት አለመቻል ትልቁ ችግር መሆኑን ሰምተናል።
ቁምነገር አየለ
ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም
