ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ ሦስት ብፁዓን አባቶች ኢትዮጵያ ገቡ።

ውጭ ሀገር የነበሩና ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተከልክለው የነበሩ ሦስት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገቡ።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ
ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል።

ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ አቡነሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍና ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *