ትራምፕ አስፈላጊ ከሆነ በዩክሬን ድርድር ለመሳተፍ ግንቦት 8 ወደ ኢስታንቡል ለመሄድ ዝግጁ ነኝ አሉ

በመካከለኛው ምስራቅ የአራት ቀናት ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኢስታንቡል ለሰላም ንግግሩ ሊቀኑ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰተዋል፡፡

በኳተር የሚገኙት ትራምፕ ስለድርድርድሩ ተጠይቀው ጦርነቱ መቆም ስላለበት ሩሲያ እና ዩክሬን “አንድ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ” የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ትራምፕ አክለውም “[ጦርነቱ] እንዲያበቃ እንፈልጋለን እና ይህን ለማድረግ እድሉ እንዳለን አስባለሁ ብለዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ቱርክ ኢስታምቡል ውስጥ በሚካሄደው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን የተመለከተ የሰላም ንግግር ላይ እንደማይገኙ ቀደም ብሉ ተገልጹ ነበር፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በንግግሩ ላይ መሪዎች እንዲገኙ ጥያቄ ቢያርቡም ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ የሩሲያ ልዑክ የሚመራው በፑቲን ረዳት ቭላድሚር ሜዲኒስኪ መሆኑን አመለክቷል።

ቀደም ሲል ቭላድሚር ፑቲን በሰላም ንግግሩ ላይ የሚገኙ ከሆነ ዜሌንስኪ እራሳቸው እንደሚሳተፉ እና ከፑቲን ጋር ለሚደረግ የፊት ለፊት ንግግር ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀው ነበር።

እ.ኤ.አ በ2022 በሀገራቱ መሃከል የተደረገው ድርድር በተመሳሳይ ስፍራ መካሄዱ ይታወሳል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *