እስራኤል፤ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ ባልታየ መልኩ በጋዛ የሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፍልስጤማውያን ነዋሪዎች አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላለፈች።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት፤ አብዛኛው ክፍሉ ቀድሞውንም በፈንጂዎች የወደመውን የጋዛ ከተማ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ብሎ የበየነ ሲሆን፣ ከተማዋ ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎችም ሊፈጸም ከታቀደው “ከፍተኛ ጥቃት” በፊት ለራሳቸውን ደኅንነት አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ተናግሯል።
በእስራኤል ከተለዩት ህንጻዎች መካከል እስላሚክ ዩኒቨርሲቲ፣ አል ሺፋ ሆስፒታል እና ሦስት የቀድሞ ትምህርት ቤቶች ይገኙበታል።
እስራኤል፤ ሐማስ እነዚህን ህንጻዎች “ማዘዣ እና መቆጣጠሪያ” ማዕከላት አድርጎ እየተጠቀመባቸው እንደሆነ በመጥቀስ ትከስሳለች። የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የእርዳታ ድርጅቶች በበኩላቸው እነዚህ ስፍራዎች ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን መጠለላቸውን ተናግረዋል።
ሰዎች ከእነዚህ ቦታዎች እንዲለቅቁ ለማድረግ ጊዜ እንደሚያስፈልግም የገለጹ ሲሆን፣ ውሳኔው ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።
ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
