የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ቱርክ ኢስታምቡል ውስጥ በሚካሄደው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን የተመለከተ የሰላም ንግግር ላይ እንደማይገኙ ተገለጸ።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በንግግሩ ላይ መሪዎች እንዲገኙ ጥያቄ ቢያርቡም ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ የሩሲያ ልዑክ የሚመራው በፑቲን ረዳት ቭላድሚር ሜዲኒስኪ መሆኑን አመለክቷል።
ቀደም ሲል ቭላድሚር ፑቲን በሰላም ንግግሩ ላይ የሚገኙ ከሆነ ዜሌንስኪ እራሳቸው እንደሚሳተፉ እና ከፑቲን ጋር ለሚደረግ የፊት ለፊት ንግግር ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀው ነበር።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ኢስታምቡል የሚገኙ ከሆነ የአሜሪካው ፕሬዝዳንትም ሊገኙ እንደሚችሉ ፍንጭ ተስጥቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ትራምፕ በንግሩ ላይ እንደማይሳተፉ ተገልጿል።
ነገር ግን የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ ውስጥ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይብ ኤርዶዋን ጋር ይገናኛሉ ተብሏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
