በአሜሪካ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ሰራተኞች የሆኑ ሁለቱ ግለሰቦች በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የአይሁድ ሙዚየም በር ላይ ነው የተገዱሉት ብለዋል የሀገሪቱ ባለስልጣናት ፡፡
ሟቾቹ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት፤ የተተኮሰባቸው በ’ካፒታል ጂዊሽ ሙዚየም’ ውስጥ ከተዘጋጀ ዝግጅት እየወጡ በነበረበት ሰዓት እንደሆነ ምንጮች በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ተናግረዋል።
ጥቃቱ የታቀደ እንደሚመስልም አክለዋል።
ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ገደማ ላይ ግድያ የተፈጸመበት አካባቢ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ሙዚየሞች የሚገኙበት ሲሆን የኤፍቢአይ የዋሽንግተን የመስክ ቢሮን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶችም ይገኙበታል።
ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ግድያው በተፈጸመበት ሰዓት በርካታ የእስራኤል ኤምባሲ ሰራተኞች ሙዚየሙ ውስጥ ኹነቱን እየታደሙ ነበር።
ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም
