የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደቡብ አፍሪካ “ነጮችን እያሳደደች ነው ” ሲሉ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳን በዋይት ሃውስ በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅሰዋል።
ደቡብብ አፍሪካ ለዘመናት የቆየ የመሬት ኢ-ፍትሃዊነትን ለመቅረፍ አልሟል ያለችውን የመሬት ፖሊሲ ማውጣቷን ተከትሎ ከአሜሪካ ጋር እየተወዛገበች ትገኛለች።
የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማሻሻል ወደ አሜሪካ ያቀኑት ሲሪል ራማፎሳ በደቡብ አፍሪካ ነጮች አርሶ አደሮች እየተገደሉ እንዲሁም እየተሳደዱ ነው በሚል ትራምፕ በጋራ ጋዜጣ መግለጫቸው ላይ ሊያፋጥጧቸው ሞክረዋል።
በዚህ ሳምንት ረቡዕ አሜሪካ ወደ 60 ለሚጠጉ ‘አፍሪካነርስ’ ተብለው ለሚጠሩት የደቡብ አፍሪካ ነጮች ጥገኝነት ከሰጠች ከሳምንት በኋላ ነው ራማፎሳ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማደስ ወደ ዋይት ሃውስ ያስቀኑት።
ነገር ግን ፕሬዚዳንት ትራምፕ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ “በነጮች ላይ የዘር ፍጅት” እየተፈጸመ ነው በሚል በመሪዎቹ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማስረጃ ያሉትን ቪዲዮ እንዲታይ አድርገዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም
