ዩክሬን ላደረሰችው የድሮን ጥቃት ፑቲን የበቀል እርምጃ እንደሚወስዱ ትራምፕ አስጠነቀቁ

ዩክሬን በሩስያ የአየር ኃይል ሰፈሮች ላይ ላደረሰችው ጥቃት ፑቲን የበቀል እርምጃ እንደሚወስዱ መናገራቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንትንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጹ።

ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ቆይታ የነበራቸው ዶናልድ ትራምፕ “ፑቲን በቅርቡ የሩስያ አየር ኃይል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ መወስድ አለብኝ ሲል አስረግጦ ነግሮኛል” ብለዋል።

የሩስያ ባለስልጣናት የትራምፕ አስተያየት እውነትነት ላይ አስተያየት ለመስጠት ቢቆጠቡም ቀደም ብሎ ሞስኮ ዩክሬን ላደረሰችው ጥቃት ወታደራዊ አጸፋ አንዱ አማራጭ መሆኑን ገልጻ ነበር።

ትራምፕ ከፑቲን ጋር ካደረጉት ከአንድ ሰዓት በላይ የፈጀ የስልክ ንግግር በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያ ባሰራጩት መልዕክት በሩስያ እና ዩክሬን መካከል ግጭት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሰላም የሚመራ አይደለም ብለዋል።

የሩስያ መንግሥት የዜና አግልግሎት እንደዘገበው ከሆነ “ዩክሬን ድርድሩን ለማወክ እየሞከረች ነው” ሲሉ ፑቲን ለትራምፕ ተናግረዋል።

ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *