ትራምፕ እስራኤል በኢራን ኢላማዎች ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ያውቁ እንደነበር ገልጸዋል፡፡የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጥቃቱ ለእርሳቸው አስገራሚ እንዳልነበረ ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቴህራን እና በሌሎች የኢራን ከተሞች ላይ ያነጣጠረ የእስራኤል መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃትን ተከትሎ ኢራን ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንደምትመለስ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
እስራኤል በኢራን ላይ የወሰደችውን ጥቃት ተከትሎ ትራምፕ ካቢኔያቸውን ለስብሰባ ጠርተዋል።
አሜሪካ በጥቃቱ አልተሳተፍኩም ወይም ለእስራኤል ድጋፍ አልሰጠሁም ትላለች።
ኢራን ከ100 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፏን የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አስታውቀዋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡
ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም
