እስራኤል የኢራኑን የበላይ መሪ ለመግደል የነበራትን እቅድ ትራምፕ ውድቅ ማድረጋቸው ተሰማ

የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል የኢራኑን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኼሜኒን ለመግደል የነበራትን እቅድ ውድቅ ማድረጋቸውን ሦስት ባለስልጣናት ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ኒውስ ገለፁ።

እንደ አንድ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ ትራምፕ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ኼሜኒን መግደል “ጥሩ ሀሳብ አይደለም” ሲሉ ነግረዋቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በዚህ መረጃ ላይ በይፋ የሰጡት አስተያየት የለም።

በሁለቱ መሪዎች መካከል ውይይቱ የተካሄደው እስራኤል በኢራን ላይ አርብ ጥቃት ከከፈተች በኋላ ነው ተብሏል።

ኔታንያሁ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወቅት ትራምፕ አያቶላህን ለመግደል የነበራቸውን እቅድ ውድቅ ማድረጋቸውን ሮይተርስ መዘገቡን ቢጠየቁም በቀጥታ ከማረጋገጥ ወይም ከማስተባበል ተቆጥበዋል።

ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *