25 የኢትዮጵያ ከተሞች “የ5G” ና ከ700 በላይ የሚሆኑት “የ4G” ኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆናቸው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ

ፍሬሕይወት ታምሩ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሚያዘጋጀው “ስለ ኢትዮጵያ” የውይይት መድረክ ላይ እንደገለፁት 52 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን የኢንተርኔት አገልግሎት በማግኘት ላይ ይገኛሉ።

አክለውም አሁን ላይ 92 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ የሀገሪቱ የቴሌኮም መሠረተ ልማት 99 በመቶ የሚሆነውን ጂኦግራፊያዊ አካባቢ ይሸፍናል ብለዋል።

ሥራ አስፈፃሚዋ የሀገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚ በአሁኑ ወቅት ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የ8 በመቶ ድርሻ ይይዛል በማለት፤ እንደማሳያ የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ መድረክ የሆነው ቴሌብር ከ53 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ማፍራቱን አብራርተዋል።

ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *