እቃ መጫኛዎቹን ከሜዲትራኒያን የባሕር ትራንስፖርት ኩባንያ ጋር በመተባበር ከጅቡቲ ወደብ ወደ እንዶዴ ባቡር ጣቢያ ማጓጓዙን አስታውቋል፡፡
ኮንቴነሮቹ ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና፣ እህል እና ሌሎች ለውጭ ገበያ ለሚቀርቡ ምርቶች የሚያገለግሉ ሲሆን የሀገር ውስጥ አምራቾች እና ላኪዎች ምርት ለዓለም አቀፍ ገበያ እንዲደርስ በማድረግ የኢትዮጵያን የውጭ ገበያ ኢኮኖሚ ይደግፋሉ ተብሏል።
በተጨማሪም ላኪዎች በጅቡቲ ወደብ የኮንቴነር አገልግሎት ለማግኘት የሚባክንባቸውን ጊዜና ወጪ ያስቀራል ሲል የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።
ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
