ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 1መቶ44 ፍልስጤማውያን በጋዛ ተገድለዋልተባለ

የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ቢያንስ 1መቶ44 ሰዎች ህይወታቸዉ ማለፉን አስታዉቋል፡፡

ከሟቾቹ በተጨማሪ 5መቶ60 ፍልስጤማዊያን ቆስለዉ ወደ ሆስፒታሎች መድረሳቸዉን ገልጿል፡፡

አጠቃላይ ጉዳቱ ከፍርስራሽ ስር የተገኙ አራት አስከሬኖችን ያጠቃልላል ተብሏል።

እስራኤል በመጋቢት ወር ከሃማስ ጋር የተስማማችውን ስምምነት ካፈረሰች ወዲህ ከ5 ሺህ ፍልስጤማውያን በላይ ሲገደሉ፤ከ17 ሺህ 8መቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል።

እስራኤል በቀይ ቀጣና ውስጥ እንደሚገኙ በመግለጽ ለሆስፒታሎች የተመደቡ የነዳጅ ማከማቻ ቦታዎችን ዓለም አቀፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት እንዳያገኙ በድጋሚ እየከለከለች መሆኗን ሚኒስቴሩ አስታዉቋል፡፡

እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለጻ፤በሆስፒታሎች ውስጥ ያለው የነዳጅ አቅርቦት ከሶስት ቀናት በላይ የማይቆይ ነዉ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ሐመረ ፍሬዉ

ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *