“እስራኤል በምትፈፅመው ጥቃት አሜሪካ የምትሳተፍ ከሆነ ‘ሲኦል’ ይፈጠራል” የኢራን ባለሥልጣን

እስራኤል በኢራን ላይ በምትፈፅመው ጥቃት አሜሪካ እጇን የምታስገባ ከሆነ በአጠቃላይ በቀጠናው ገሃነም እንደሚፈጠር የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለቢቢሲ ተናገሩ።

“ይህ የአሜሪካ ጦርነት አይደለም” ያሉት ሳኢድ ኻቲብዛዴህ፣ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ከተሳተፉ በማይመለከታቸው ጦርነት ውስጥ የገቡ ፕሬዚደንት ሆነው ሁል ጊዜም ይታወሳሉ ብለዋል።

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጨምረውም የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ግጭቱን ወደ “አረንቋነት” እንደሚለውጠው፣ ቁጣው ተባብሶ እንደሚቀጥል እና የሚፈፀመውን ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ማብቂያ እንደሚያዘገየው ተናግረዋል።

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በኢራን የሚሳኤል ጥቃት በደቡባዊ እስራኤል የሚገኘው ሶሮካ ሆስፒታል ከተመታ በኋላ ነው።

የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ጥቃቱ ሆስፒታሉን ሳይሆን ከሆስፒታሉ አጠገብ የሚገኝ ወታደራዊ ሥፍራን ዒላማ እንዳደረገ ዘግበዋል።

ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *