የአሜሪካ ምክር ቤት አባሏ ትራምፕ ግጭቱን የያዙበት መንገድ “እጅጉን አሳስቦኛል” አለች

የአሜሪካ ኮንግረስ አባል የሆነችው ትውልደ ኢራናዊት እና ዲሞክራቷ ያሳሚን አንሳሪ፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእስራኤል እና የኢራን ግጭትን ያስተናገዱበት መንገድ “እጅግ አሳስቦኛል” አለች።

ለቢቢሲ ኒውስዴይ ፕሮግራም “በየቀኑ ሀሳቡን የሚቀይር ፕሬዝዳንት ነው ያለን” ያለች ሲሆን፣አክላም “የሚናገረውን ማንም አያምንም” ነው ያለችው ።

የኢራቅ ጦርነትን በመጥቀስ ዩናይትድ ስቴትስ በቀጠናው ጥሩ ወይም “የተሳካ” ታሪክ ስለሌላት ጣልቃ መግባት እንደሌለባት ተናግራለች።

አንሳሪ ኢራናውያን ሥልጣን ላይ ያለው አካል አለመሆናቸውን ማስታወሱ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቅሳ፣ አብዛኛው ሕዝብ ከ1979 ጀምሮ “በዕገታ ውስጥ” የያዛቸውን እስላማዊ ሪፐብሊክ እንደሚቃወሙ ገልጻለች።

በመሆኑም “በአገራቸው በቦምብ መደብደብ አይገባቸውም” ብላለች።

ትራምፕ ግጭቱን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እና የአሜሪካ ወታደሮች “አላስፈላጊ የሕይወት መጥፋት” ወደ ሚወስድ መንገድ ላይ እንዳያተኩሩ አሳስባለች ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *