የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ኘሮጀክት በበጀት አመቱ እንዲጠናቀቅ ቢታቀድም አለመጠናቀቁ ተገለፀ

የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ኘሮጀክት 78 በመቶ የሲሚንቶ እጥረት ያጋጥመዉ እንደነበር ሰምተናል።

ይህ የደረቅ ወደብ ኘሮጀክት ከፍተኛ መጓተት የተስተዋለበት እንደሆነ ተገልፆል።

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር የ11 ወራቱን የስራ አፈፃፀም ባቀረበበት ወቅት የከተማ እና መሰረተ ልማት  ቋሚ ኮሚቴ  የሎጀስቲክ መሰረተ ልማት ኘሮጀክቶች ዙሪያ ጥያቄ አቅርቧል።

ቋሚ ኮሚቴዉ የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ኘሮጀክት በበጀት አመቱ እንዲጠናቀቅ ቢታቀድም አለመጠናቀቁ አሳዉቋል።

ኮሚቴዉ የማስፋፊያ ኘሮጀክቱ መዘግየት ምክንያት ምን እንደሆነ እና ለማጠናቀቅ እንዲቻል የተቀመጡ አቅጣጫዎች ምን እንደሆኑ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጠይቋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ የሰጡት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ የኘሮጀክቱን መጓተቱን እንደሚቀበሉ ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ እንደምክንያትነት ያስቀመጡት የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ኘሮጀክት 78 በመቶ የሲሚንቶ እጥረት ያጋጥመዉ እንደነበር በማንሳት ነዉ።

የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር እንዲጓተት ምክንያት እንደሆነ የገለፁት ሚኒስትሩ ይሄ ወደብ ከባድ የሆኑ ማሽነሪዎች የሚንቀሳቀሱበት በመሆኑ መሠረቱን ጨምሮ ግንባታዉ ክብደት በሚችል መልኩ መገንባት የሚያስፈልገዉ ሆኗል ብለዋል።

ይህን ለማድረግ በሲሚንቶ እንዲገነባ የሚጠየቅ ሆኗል በርካታ የሲሚንቶ አቅርቦት የሚጠይቅም ነዉ ብለዋል ሚኒስትሩ።

የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት ለዚህ ግንባታ በቀን ከሚያስፈልገዉ የሲሚንቶ አቅርቦት ዉስጥ 22 በመቶ ብቻ ሲቀረብ እንደነበር ተገልፆል።

የዚህ ፋብሪካ ስራ መጀመር የሲሚንቶ የአቅርቦት እጥረቱን እና የዋጋ ችግሩን የፈታ መሆኑን ዶ/ር አለሙ ስሜ ተናግረዋል።

የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ኘሮጀክት ለመጓተቱ የኮንትራክተር የገንዘብ ፍሰት ችግር ነዉ ብለዋል።

ይህንን ችግር ለመፍታት ኮሜቴ በማቋቋም ለስራው የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማሪታይም ባለስልጣን የሚገዛውን እየገዛ እና እያቀረበ ስራዉ እንዲሰራ ተደርጓል ተብሏል።

ሚኒስትሩ በመሆኑም የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ኘሮጀክት በሶስት እና በአራት ወራት ዉስጥ እንጨርሳለን ብለን እናስባለን ብለዋል።

በ2011 ዓ. ም ስራዉ የተጀመረዉ የፕሮጀክቱ ማስፋፊያ በሦስት ዓመት እንደሚጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞለት ነበር።

ቁምነገር አየለ

ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *