የእስራኤል የመከላከያ ሃይሎች ዋና አዛዥ ኢያል ዛሚር እንዳሉት ለ12 ቀናት በዘለቀው ጦርነት የእስራኤል የምድር ኮማንዶ አባላት በኢራን ውስጥ በድብቅ ስራዎችን ሲሰሩ ነበር ብለዋል።
የኮማንዶ አባላቱ ከእስራኤል አየር ሃይል ጋር በመናበብ እስራኤል የኢራንን የአየር ክልል እና ሌሎች አካባቢዎችን እንድትቆጣጠር ትልቁን ስራ ሲሰሩ እንደነበር የጦር አዛዡ ገልጸዋል።
አዛዡ እንዳሉት እነዚህ ስኬቶች ሊገኙ የቻሉት ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ በአየር ሃይሎች እና በመሬት ላይ በነበሩት የእስራኤል የኮማንዶ አባላት በተደረገው ውህደት ነበር ብለዋል፡፡
ገነነ ብርሃኑ
ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
