የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ሃላፊ ቶም ፍሌቸር በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጉብኝታቸውን ያደረጉ ሲሆን በተለይም ግጭት የተከሰተባቸውን የ ሃገሪቱን ምስራቃዊ ክፍሎች ጎብኝተዋል።
አሁን ላይ በኮንጎ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልፀዋል።
የ ተባበሩት መንግስታት የ እርዳታ ሃላፊው ቶም ፍሌቸር በዲሞክራቲክ ኮንጎ በርከት ያሉ ከተሞችን የጎበኙ ሲሆን በሃገሪቱ ሰብአዊ ፍላጎቶች ላይ ለመወያየት ማህበረሰቦችን እና የሰብአዊ እርዳታ አጋሮች ጋር ውይይት አድርገዋል ።
በምስራቅ ኮንጎ እየተንቀሳቀሱ ያሉት የኤም 23 አማፂያን ከታህሳስ ወር ጀምሮ የጎማ እና የቡካቩ ዋና ከተሞችን እንዲሁም ሰሜን እና ደቡብ ኪቩን ጨምሮ ስልታዊ አካባቢዎችን በቁጥጥራቸው ስር አድርገዋል።
የኮንጐ መንግስት ጎረቤት ሩዋንዳ በምስራቃዊ ኮንጎ የሚዋጉትን M23 አማፂያንን ትደግፋለች ሲል ክስ ቢያቀርብም ሩዋንዳ ክሱን አስተባብላለች።
እስካሁን በኮንጎ የ እርስበርስ ግጭት ከ 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል ዘገባው የአናዱሉ ነው ፡፡
ገነነ ብርሃኑ
ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
