በተባበሩት መንግስታት የአደንዛዥ እፅ እና የወንጀል ፅህፈት ቤት ይፋ እንዳደረገው የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም እና ህገወጥ ዝውውር በአለም አቀፍ ደረጃ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል ብሏል።
ይሄንንም ተከትሎ በአለም ላይ አለመረጋጋቶች እየተባባሱ በመምጣታቸው እና የተደራጁ ወንጀሎች መስፋፋታቸውን አስታውቋል።
የዓለም የመድኃኒት ሪፖርት እንደሚያሳየው የተደራጁ የዕፅ አዘዋዋሪ ቡድኖች ዓለም አቀፍ ቀውሶችን መጠቀማቸውን እና ለችግር የተጋለጡ ሰዎችን ማነጣጠር ቀጥለዋል ሲሉ በተባበሩት መንግስታት የ አደንዛዥ እፅ ቁጥጥር ሥራ አስፈፃሚ ጋዳ ዋሊ ተናግረዋል።
በመከላከል ላይ ኢንቨስት ማድረግ እና የአደንዛዥ እፅ ንግድ መንስኤዎችን የአቅርቦት ሰንሰለቶችን በመለት መከላከል አለብን ሲሉ ሃላፊው ገልፀዋል።
በ 2023 በተቀመጠ ግምት 316 ሚሊዮን ሰዎች አደንዛዥ እፅ ይጠቀማሉ ወይም ተጠቅመዋል።
ይሄም ከአለም ህዝብ 6 በመቶ ይይዛል።
ተጠቃሚዎቹም ከ 15 እስከ 64 አመት ያሉ መሆናቸውን የሚገልፀው ሪፖርቱ በብዛት ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት አደንዛዥ እፆችም ኮኬይን ቀዳሚውን ቦታ ይዟል።
የኮኬይን አዘዋዋሪዎች በመላው እስያ እና አፍሪካ አዳዲስ ገበያዎችን እየፈጠሩ እንደሆነ በሪፖርቱ ተገልጿል።
በተለይም ሁከት ባለባቸው ሃገራት በጣም የት እፅ መስፋፋቱ ጨምሯል ሲል ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
ገነነ ብርሃኑ
ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
