የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር መንግስታቸው ለኔቶ መከላከያ ጦር ወጪ ይልቅ ለሀገራቸው ብሄራዊ ጥቅምና መከላከያ ቅድሚያ እንደሚሰጡ ገለጹ

የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር አንቶኒ አልባኔስ ይሄንን ያሉት አውስትሊያ ለኔቶ ጦር የምታዋጣውን ገንዘብ ከፍ እንድታደርግ ከአሜሪካ ጫና እየተደረገባት እንደሆነ ከገለጹ በኋላ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አውስትራሊያ ለራሷ ብሄራዊ ጥቅምና መከላከያ ጦሯ ቅድሚያ እንደምትሰጥ ከገለጹ በኋላ ለረጅም ጊዜ እቅድና ስራዎች 57 ቢሊየን ዶላር ላጭር ጊዜ ስራዎች ደግሞ 10 ቢሊየን ዶላር በበጀታቸው ላይ መጨመራቸውን ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ኔቶ ብዙ ክፍሎቹን ለማሳደግ ባወጣው እቅድ መሰረት የኔቶ አባል ሃራቱ ለጦሩ የሚያዋጡትን የገንዘብ መጠን ጨምረዋል፡፡ምንም እንኳን አውስትራሊያ በይፋ የኔቶ አባል ባትሆንም ከኔቶ አባል ሀገራት ጋር በጋራ ትሰራለች፡፡

እናም ለኔቶ የምታደርገው ድጋፍ እንዲጨምር ከአሜሪካ እየደረሰባት ላለው ጫና ጠቅላይ ሚንስር አንቶኒ አልባኔዝ ሀገሪቱ ለራሱዋ ጉዳዮች ቅድሚያ ትሰጣለች ብለዋል፡፡

ስፔንም አዲሱን የገንዘብ መዋጮ በመቃወም አልተቀበለችውም በዚህም ዶናልድ ትራምፕ ሃገሪቱን በቀረጥ እንደሚቀጧት ገልጸዋል ሲል አናዱሉ ዘግቧል፡፡

ገነነ ብርሃኑ

ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *