የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤላውያንና የአይሁድ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና እና ልዩነቶችን ችላ ብሏል ሲሉ የሀርቫርድ ዩንቨርስቲን ከሰሱ።

አስተዳደራቸዉ ለዩኒቨርሲቲዉ የሚሰጠዉን የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ እንደሚያቋርጥም ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በተማሪዎች ላይ እየደረሰ ላለው እንግልት በቂ ምላሽ እየሰጠ አይደለም ያሉትን የሀርቫርድ ዩንቨርሲቲ የነጻነት መብት ተሟጋች ቢሮን ከሰዋል፡፡

የጤና እና ሰብዓዊ አገልግሎት ተቋም ባደረገው የፌዴራል ምርመራ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ከአድሎና ጥቃት ለመከላከል ያደረገው ጥረት አነስተኛ እንደሆነ አሳይቷል ነዉ ያሉት፡፡

ሃርቫርድ ዩንቨርሲቲም ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለው ጥረት ዝቅተኛ ነዉ ብለዋል፡፡

አስተዳደሩ ለዩንቨርሲቲው የሚሰጠውን የፌደራል ገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ እንደሚያቋርጥና የተወሰነ የገንዘብ ድጋፎችም እንደታገዱ ገልጸዋል፡፡

ለዩኒቨርሲቲዉ ይዉል የነበረው በቢልየን የሚቆጠር ዶላር ጠቃሚ የምርምርና የተማሪ ፕሮግራሞችን ለመደገፍ ይውላሉ ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና አስተዳደራቸው፤ ትምህርት ቤቶች ሁሉንም ተማሪዎች ከአድሎ ለመጠበቅ የበለጠ መስራት አለባቸው ብለዋል።

አንዳንድ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች መንግስት እነዚህን ምርመራዎች እያደረገ ያለው ትምህርት ቤቶችን ለመቆጣጠር እና የሰዎችን የመናገር ነጻነት ለመገደብ እንደሆነ ያምናሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሃርቫርድ ዩንቨርሲቲ ለዚህ ክስ እስካሁን ምንም ምላሽ ያልሰጠ ሲሆን፤ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በዩኒቨርሲቲው ላይ ተጨማሪ እርምጃዎች ሊወሰዱ እንደሚችሉ እየተገለጸ ይገኛል ሲል ፍራንስ 24 ነዉ የዘገበዉ።

ኤርሚያስ ገረመዉ

ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *