መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአሜሪካ-እስራኤል የሚደገፈውን የጋዛ የዕርዳታ ሥርዓትን ተመድ እንዲተካ ጠይቀዋል፡፡

ከ1መቶ በላይ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጋዛ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ እየጠየቁ ነው፡፡

የእስራኤል የማከፋፈያ ዕቅድ ገዳይ ነዉ ስለዚህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚመራው የዕርዳታ ማስተባበር ወደ ስራዉ ይመለስ በማለት በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።

የእርዳታ ማከፋፈያ ቦታዎች ቁጥር ከ4መቶ ወደ አራት በወታደራዊ ሃይሎች ቁጥጥር ወደሚደረግባቸዉ ቦታዎች ዝቅ ብሏል ሲል ቡድኑ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በአሜሪካ እና እስራኤል የሚደገፈው የጋዛ ሰብአዊ ፋውንዴሽን (GHF) ፤በጋዛ የሚገኙ ሁለት ሚሊየን ሰዎች በተጨናነቁ ወታደራዊ ዞኖች ዉስጥ ምግብ ለማግኘት ሲሞክሩ በየቀኑ የተኩስ እና የጅምላ ጉዳት ሰለባ እንዲሆኑ አስገድዷቸዋል ሲል አክሏል፡፡

መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶቹ በመግለጫቸዉ፤ የሰብዓዊ ፋዉንዴሽኑ ወደ ስራ የገባዉ የተስፋ መቁረጥ፣ የአደጋ እና የሞት ዑደትን ለማስቀጠል ነው ሲሉ ከሰዋል።

የእስራኤል ባለስልጣናት በእርዳታ እና በንግድ እቃዎች ላይ በድጋሚ አጠቃላይ እገዳን ካደረጉ ከ1መቶ ቀናት በላይ ተቆጥረዋል ብለዋል፡፡

ከግንቦት 27 ጀምሮ በ GHF በሚተዳደሩ የእርዳታ ማከፋፈያ ቦታዎች ምግብ በመጠበቅ ላይ የነበሩ 6መቶ የሚደርሱ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከ4 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

እስከዳር ግርማ

ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *