የፌዴራል ዋና ኦዲተር ከሰሞኑ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ያቀረበዉ የፌደራል ባለ በጀት መስራቤቶች የ2016 በጀት አመት የኦዲት ሪፖርት በርካታ ግኝቶችን ያካተተ ነበር ፡፡
በዚህ ሪፖርት ላይ በ2016 በጀት አመት ከ185 የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የ169ኙን የፋይናንስ ህጋዊነት ኦዲት መስራቱን የገለፀዉ ዋና ኦዲተር ከ2015 ግኝቶች ዉስጥ እርምጃ ያልተወሰደባቸዉ አካቷል።
በዚህም እንዲመልስ አስተያየት ከተሰጠበት 20 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር እና 23ሺህ 2መቶ 30 ዶላር ዉስጥ የተመለሰዉ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር እና 30 ዶላር ብቻ እንደሆነ በሪፖርቱ አመላክቷል ፡፡
የመለሱትም አምስት የገቢዎች ሚኒስተር እና 4 የጉምሩክ ኮሚሺን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች እንዲሁም ዉልቂጤ እና ሃሮሚያ ዩኒቨርስቲ ብቻ መሆናቸዉን ሪፖርቱ ዘርዝሯል ፡፡
የቀረዉ 17 ነጥብ 5ቢሊዮን ብር እና 23ሺህ 2መቶ ዶላር እርምጃ ሳይወሰድበት ቀጣዩ በጀት አመት እየተጠናቀቀ ይገኛል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
