የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ ቀጣይ የሊጉን አካሄድ በተመለከተ ተከታዩን ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛል።
“ሊጉ በምን መልኩ (ፎርማት) ይቀጥላል የሚለውን እየተነጋገርን ነው። ይሄ አካሄድ ከኮቪድ በኋላ ነው የሆነው። ከዛ በኋላ ፎርማቱ በዛው ቆሟል።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ የማታከናውንባቸው ሁኔታዎች አሉ።
በቀጣይ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬችን ስር የሚደረጉ ውድድሮች እንዳለፉት አመታት በአንድ ቦታ አይከናወኑም።
ክለቦች የሚቀርባቸውን የተሻለ ሜዳ አስመዝግበው እየተመላለሱ የሚጫወቱበትን መንገድ እያመቻቸን ነው። ሊጉንም በተመለከተ ንግግር እያደረግን ነው።” በማለት የሊጉ ቅርፅ ለውጥ ሊደረግበት እንደሚችል ጥቆማ አድርገዋል
“ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት እንደሌለው ልንገነዘብ ይገባል ፣ አንድን ክለብ ለመጥቀም ሌላውን ለመጉዳት የተደረገ ውሳኔ አይደለም “ ብለዋል አቶ ኢሳያስ ጅራ፡፡
ጋዲሳ መገርሳ
ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
