የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው ዕለት መወሰናቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በ2017 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ በተማሪዎች ውጤት ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
በ2017 ዓ.ም 79,034 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን የቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ገልጸዋል፡፡
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።
ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
