የድጅታል የክፍያ የገንዘብ ዝውውር 12.5 ትሪሊዮን መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

በጠቅላላው ሲታይ የፋይናስ ዘርፉ አድጓል ማለት ይቻላል ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ለመጀመሪያ ጊዜ ከእጅ በእጅ ግብይት በላይ የድጅታል ግብይቱ በልጦ ተገኝቷል ብለዋል።

የድጅታል የክፍያ የገንዘብ ዝውውር 12.5 ትሪሊዮን መድረሱን ገልፀው፤ይህ የሚያመላክተው የካሽ ስርዓቱን ምን ያህል ድጅታል ዘርፉ እንደ በለጠው ማሳያ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

በብድር ደግሞ 11 ሚሊዮን የሚጠጉ አነስተኛና ጥቃቅን ተበዳሪዎች 24.5 ቢሊዮን ብር የእጅ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ብድር ማግኘት ችለዋ ብለዋል።

ጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ ይደርስ የነበረው የብድር ስርጭት ለብዙዎች እንዲደርስ ማድረግ ተችሏል ነው የተባለው።

ለዚህም ምክንያቱ በማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው መንግስት ከንግድ ባንክ፤በፊት በቦንድና በተለያዩ መንገዶች ከ850 እስከ 900 ቢሊዮን ብር ይበደር የነበረውን በማቆሙ ነው ብለዋል።

ሆኖም በኢኮኖሚ ማሻሻው ምክንያት ከባንኩ ያለመበደሩ ባንኩ እንዳይጠፋና የፋይናስ ዘርፉም አንዳይጎዳ አድርጎታል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሃገሪቱ የፍይናስ ሴክተር ምሶሶ ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናግረዋል።

ልኡል ወልዴ

ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *