ባለፈው አመት 26 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ እንደነበር እና በዘንድሮ አመት ግን 31.8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ማረስ መቻሉን አሰታውቀዋል፡፡
ይህል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአባላቱ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት ነው፡፡
ይህም ካለፈው የበጀት አመት ጋር ሲነጻፀር 5.8 ሚሊዮን ሄክታር ተጨማሪ ቦታ መታረሱን ያሳያል ብለዋል፡፡
እንዲሁም በ2017 አ.ም 3 መቶ ሚሊዮን ኩንታል ጨምሮ 1.5 ቢሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰብ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዘርፉ 24 . 7 ፐርሰንት ከአምና ዘነድሮ እድገት እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስተሩ አስታውቀዋል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
