ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላቱ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ነው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ጥያቄዎች

መንግስት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንዳለ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ከቤት ፈላጊው ቁጥር ጋር ተነጻጽሮ ሲታይ ገና ብዙ ስራ ይጠይቃል። ምን አይነት ስራዎች እተሰሩ ነው?

የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና ከተፈጠረባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የመንግስት ሰራተኛው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡

በዚህ ምክንያት በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ፡፡ የመንግስት ሰራተኛን የኑሮን ደራጃን ከማሻሻል አኳያ ምን እተሰራ ነው?

ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ እቅድ አፈጻጸም ከቁልፍ የኢኮኖሚ እድገት አመላካቾች አንጻር በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማብራያ ቢሰጥ?

የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የስራ አፈጻጻም እንዲሁም የተቀረውን የትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ በምን ምለኩስ ለማካሄድ ታስቧል፡፡

ሀገራዊ የስቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስኬታማ እንዲሆን የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን

የዳሰነች ወረዳን አሁን ያለበትን የተፈጥሮ አደጋ ችግር መጋረጥን በተመለከተ መነግስት እንዲሁም የክልሉ መንግሰት እያደረገ ያለውን ለውጥ በተመለከተ ምላሽ ቢሰጥበት

በሃገሪቱ አንዳነድ አካባቢዎች ባልተጠበቀ መልኩ ወረርሺኞች እየተከሰቱ ይገኛሉ እና እሱሀን ለመከላከል ምን እየተሰራ ነው የሚሉ ናቸው፡፡

ለዓለም አሰፋ

ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *