የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወሳኔ!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ሰኔ 25 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  ሰኔ 24 2017 በተራ ቁጥር 3 ላይ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ውሳኔዎችን በሲዳማ ፣ በመቻል እና በሀዋሳ ከተማ ስፖርት ቡድኖች ላይ አስተላልፏል።

ሶስቱ ክለቦች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች ክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያን በመተላለፍ እግድ ከተጣለባቸው ተጫዋቾች መካከል ቢያንስ አንዱን አሰልፈው ስለማጫወታቸው በእለቱ ጨዋታውን ከመሩት ዳኞች ከቀረበው ሪፖርት  ተረጋግጦ ውሳኔዎች ተላልፈዋል።

ስለሆነም  ክለቦቹ ተጫዋቾቹን በመጠቀም ያደረጓቸውን ጨዋታዎችን በፎርፌ እንዲሸነፉ  በዚህም ለተጋጣሚዎቹ በሙሉ 3 ነጥብና 3 ንጹህ ግቦች እንዲሁም ለሶስቱ ክለቦች ደግሞ በእያንዳንዱ ጨዋታ 0 ነጥብ እና 3 የግብ እዳ እንዲመዘገብ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

በተሰጡት የፎርፌ ውሳኔዎች መሰረት  የ2017 የፕሪሚየር ሊግ ደረጃና ግብ አግቢዎች  ተስተካክሏል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ

ጋዲሳ መገርሳ

ሰኔ 27 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *