ሲንቄ ባንክ በ2024/2025 የሂሳብ ዓመት 173 በመቶ እድገት በማሳየት የባንኩን ገቢ ወደ 15 ነጥብ 4 ቢሊዮን ማድረሱን ገልጿል።
ባንኩ ይህን የገለፀው የ2024/2025 የሂሳብ አመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን በዛሬው እለት መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው ።
በመግለጫዉም የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ንዋይ መገርሳ፤ሲንቄ ባንክ እንደ ባንክ ከተቋቋመ ሥስት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣በኢትዮጰያ የባንክ ኢንደስትሪ ውስጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ታሪካዊ አፈጻጸሞችን አስመስግቧል ብለዋል ፡፡
ፕሬዚዳንቱ አቶ ንዋይ ሲንቄ ባንክ አሁን ላይ 120 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ካፒታል አለው ሲሊም ተናግረዋል።
ካለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር በዘንድሮ አመት በ99 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
አቶ ንዋይ 8 ቢሊዮን የተከፈለና 15 ቢሊዮን ያልተከፈ ካፒታል እንዳለም ጠቁመዋል ።
ባንኩ ባሉት ከ590 በላይ ቅርንጫፎቹ ለ12 ሺህ ያህል ሰራተኞች የስራ እድል ፈጥሮ እያሰራ መሆንን ገልጿል ።
ባንኩ ካለው 590 ቅርንጫፎች ውስጥ በ17 ቅርንጫፎቹ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ለሙስልሞች ብቻ ይሰጣሉ ብለዋል።
ሲንቄ ባንክ ከተለያዩ እንደ ግብርና፣ማኑፋክቸሪንግ ፣ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የኢኮኖሚ ዘርፎች የባንክ ለባንክ ብድርን ሳይጨምር 56.6 ቢሊዮን ብር ሆኖ ተመዝግቧል ብለዋል።
ልኡል ወልዴ
ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
