አዲስ አበባ በዘንድሮው በጀት ዓመት 233 ቢሊዮን ብር ስብስባለች አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በዘንድሮው በጀት ዓመቱ 241.4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ሲሆን 233 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96.5 % ማሳካት እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡

ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት 83.3 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ወይም 45 በመቶ እድገት በከተማዋ ገቢ ላይ እድገት ያሳየ ነው። ያልተሰበሰበው 8 ቢሊዮን ብር ከእርዳታ እና ብድር ይገኛል ተብሎ በተጨማሪ በጀት የታወጀ እንደነበርም አስታውሰዋል።

ለውጥና እድገት በራስ አቅም ሲሆን መሰረቱ ሰፊ፤ ምሰሶውም ጠንካራ ይሆናል ያሉት ከንቲባዋ።

ለከተማዋ ነዋሪዎች፤ ግብር ከፋዮች፤ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ለተገኘው ስኬት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባለሰፈሩት መልዕክት አመስግነዋል፡፡

ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *