አካባቢያዊ ብክለትን ለመከላከል በሁለቱ የክረምት ወራት ንቅናቄ እንደሚጀመር ተገለፀ።

በዛሬዉ እለት የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በተያዘው ሀምሌ እና በነሀሴ ወቅቶች የአፈር እና የአየር ብክለትን ለመከላከል ያግዛል የተባለ ንቅናቄ እንደሚደረግ ገልፆል።

በቀጣይ በሚኖሩ ስድስት ወራት በኘላስቲክ ብክለት÷ በአየር ብክነት ÷ በቆሻሻ አያያዝ ÷ በድምፅ ብክለት እና አካባቢና ማህበራዊ ተፅእኖ ላይ የማህበረሰብ ግንዛቤን ለመጨመር ያለመ ንቅናቄ ለማድረግ ታቅዷል ተብሏል።

ግንቦት 28 የጽዱ ኢትዮጵያ ባህል ማድረግ በሚል በተደረገው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ግንዛቤው እንዲኖራቸው እየተደረገ መሆኑን ተነግሯል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ በዚህ ንቅናቄ ከ 50 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተደራሽ የሚያደርግ ይሆናል ተብሎ እንደተገመተም ጠቁመዋል።

አካባቢን የሚበክሉ ደረቅ ቆሻሻን በተመለከተ ዜጎች ግንዛቤው እንዲኖራቸው ለማድረግ የግንዛቤ መፍጠር ስራዎች እንደሚኖር ተገልጿል።

ባለስልጣኑ ዛሬ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር የዉይይት እና የስልጠና መድረክ አሰናድቷል።

አዲስ በጸደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ዙሪያ አዋጁ ወደ ተግባር ከመዉረዱ በፊት በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት እንዲሁም የሚዲያ አካላት ጋር ውይይት እንደሚኖር ሰምተናል።

የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል የተባለው አዋጅ ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ መቀነስ እና መልሶ መጠቀም እንዲሁም በአግባቡ ማስወገድ የተመለከተ ነዉ ተብሏል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢት ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ግንዛቤው እንዲኖረው እና ተኪ ምርቶችን እንዲጠቀም ለማድረግ ያለመ ነዉ።

ማንኛውም ሰው የፕላስቲክ የእቃ መያዣ ቀረጢት ይዞ ከተገኘ ከ5,000 እስከ 10,000 የሚያስቀጣው እንደሆነ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጁ መያዙ የሚታወስ ነዉ።

ቁምነገር አየለ

ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *