አባይ ባንክ ጠቅላላ ሐብቱ 91.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገለፀ

ባንኩ የተመሰረተበትን “15ኛ ዓመትንም” በይፋ ማከበር ጀመሯል

ባንኩ የተመሰረተበትን “15” እመት የምስረታ በዓል በይፋ ማከበር መጀመሩን አስመልከቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይእንደተገለፀው፣ ከዛሬ ጀምሮ በቀጣይ በዓመቱ ባሉ ወራት የተለያዩ ሁነቶችን በማዘጋጀት ከብረ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ የሚያከብር መሆኑ አስታውቋል።

በበጀት ዓመቱ ባንኩ የተቀማጭ ገንዝብ መጠኑን ከባለፈው ዓመት መነሻ በ37% በማሳደግ ብር 72 ቢሊዮን ያደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ሐብቱም የ38% እድገት በማስመዝገብ ብር 91.3 ቢሊዮን ደርሷልም ብሏል።

ባንኩ ለተለያየ የኢኮኖሚ ዘርፍ የሰጠው ጠቅላላ የብድር መጠንም 47.4 ቢሊዮን ብር የደረሰ መሆኑ እንዲሁም ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢው የ95% እድገት በማሳየት 16.2 ቢሊዮን መድረሱ ተገልጿል።

በ823 መሰራች ባለአክሲዮኖች 125.8 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ሥራ የጀመረው ባንኩ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ አድገት በማስመዝገብ የባለአክሲዮኖችን ቁጥሩ 4,500 በማድረስ የተከፈለ ካፒታሉን 7 ቢሊዮን ብር ማድረስ ችሏል፡፡

ባንኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚጠይቀውን መስፈርት በማሟላት የባንከ አገልግሎት መሰጠት የሚያስችለውን ፈቃድ የዛሬ አስራ አምስት ዓመት ሐምሌ 7 ቀን 2002 ዓ.ም ያገኘ ሲሆን በይፋ ሥራ የጀመረውም ጥቅምት 25 ቀን 2003 ዓ.ም ለባንከ ኢንዱስትሪው 13ኛ ባንክ በመሆን እንደነበረ ለማወቅ ተቸሏል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *