ንብ ተራ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ ማዋሉን ንብ ባንክ አስታወቀ፡፡

ንብ ተራ ኦንላይን ወይም ሱፐርአፕ ከባንክ አገልግሎት በተጨማሪ ግብይቶችን እና ክፍያዎችን መፈጸም የሚያስችል ነዉ ተብሏል፡፡

የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፤ የሞባይል መተግበሪያዉ ከደህንነት አንጻርም የተለያዩ ፊቸሮች እንዳሉት ገልጸዋል፡፡

መተግበሪያዉን የባንኩ ባለሙያዎች ያበለጸጉት መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚዉ፤ በሂደት ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶች የሚካተቱበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ባንኩ አዲስ የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድና የአምስት ዓመት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ወደ ስራ መግባቱን አስታዉቀዋል፡፡

እነዚህን ዕቅዶች ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ የገባዉ የሞባይል መተግበሪያ አንዱ ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በበጀት ለሚተዳደሩ በጀታቸዉን ይቆጣጠሩበታል፣ ከባንክ ወደ ባንክ የሚተላለፉ ክፍያዎችን እና የባንኪንግ የኦፕሬሽን ስራዎች ይሰሩበታል ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ተናግረዋል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *