የአለም አቀፍ የጥበቃ ቡድን ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በጋዛ ሰርጥ በሚደርሰው ወታደራዊ ጥቃት በየቀኑ ከ10 በላይ ህፃናት አንድ ወይም ሁለቱንም እግራቸዉን ያጣሉ፡፡
ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ከ40 ሺህ በላይ ህፃናት መቁሰላቸው እና ከ 1ሺህ5መቶ በላይ የህክምና ባለሙያዎች ደግሞ መሞታቸዉን ገልጿል፡፡
ከ4መቶ በላይ የሚሆኑ በሰብዓዊ እርዳታ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ህይወት ማለፉንም የቡድኑ ሪፖርት ያመላክታል።
ሪፖርቱ አክሎም 90 ከመቶ የሚሆነው የጋዛ ህዝብ በግዳጅ እንዲፈናቀል መደረጉን ተከትሎ በተለይ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ለከፍተኛ የስነ-ልቦና ጉዳት እየተዳረጉ ነዉ ብሏል፡፡
ከጥቅምት 2023 ጀምሮ በተነሳው በዚህ ጦርነት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ከ 1መቶ 97 ሺህ በላይ የሚሆኑ ፍልስጤማዊያን እንዲሞቱ እና ጉዳት እንዲደርስባቸው ሆኗል ያለዉ ሪፖርቱ፤ከ 10 ሺህ በላይ የሆኑ ሰዎች ደብዛቸው ጠፍቶ እንደቀረ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መፈናቀላቸዉን አስታዉቋል ሲል የዘገበዉ ሚድል ኢስት ሞኒተር ነዉ፡፡
ሀሚድ አብደላ
ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
