ሚኒስትሩ የአለምአቀፉ የሚቲዮሮሎጂ ድርጅት ዋና ጸሃፊን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በነበራቸው ቆይታም ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የሚቲዮሮሎጂ አገልግሎት ለግብርና፣ የጤና የውሃ ሀብት አስተዳደር እና ሌሎች ዘርፎችን በብቃት እየደገፈ መሆኑን ጠቅሰው፤ የአየር ጸባይ ትንበያ ስራው አስተማማኝነትና ትክክለኛነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል ብለዋል፡፡
እንዲሁም ንጹህ ታዳሽ ኢነርጂ ለቀጠናው ሀገራት በማቅርብም በቀጠናው የካርቦን ልቀት መጠን ቅነሳ ላይ አስተዋጽኦ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአለምአቀፉ የሚቲዮሮሎጂ ድርጅት ዋና ጸሃፊ ፕሮፌሰር ሰለስቴ ሳዉሎ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የሚቲዮሮሎጂ አገልግሎት ያለበት ደረጃ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ዋና ጸሃፊዋ የሚቲዮሮሎጂ አገልግሎትን ለማዘመን አለምአቀፉ የሚቲዮሮሎጂ ድርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ከሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናረግዋል፡፡
ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
