ሊቨርፑል በዚህ ሳምንት መጨረሻ ዝውውሩን ለመጨረስ ፍላጎት እንዳለው በርካታ ምንጮች ጠቁመዋል።
ኒውካስትል ለኤኬቲኬ ያቀረበው £70m በኢንትራክት ፍራንክፈርት ውድቅ የተደረገ ሲሆን ሊቨርፑል ያቀረበው ጥያቄ ኒውካስትል ከቀረበው የላቀ ሆኖዋል።
የ23 አመቱ ተጨዋች ፍራንክፈርት በቡንደስሊጋው ባለፈው 2024/25 የውድድር ዘመን 3ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ በ31 ጨዋታዎች 15 ጎሎችን አስቆጥሯል።
ኤኬቲኬ በቡንደስሊጋው ባለፈው የውድድር ዘመን 117 ኳሶችን የሞከረ ሲሆን ከማንኛውም ተጫዋች በላይም ያድረጎዋል።
ሊቨርፑሎችም የኒውካስል አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳክን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል ነገር ግን የኒውካስሎች ስዊዲናዊው አጥቂ በምንም አይነት ዋጋ ላልመሸጥ ፅኑ አቋም አላቸው።
ኢኬቲኬን ለማዝዋውር ያደረጉት ሙከራ መቀዛቀዝ ተከትሎ ኒውካስትሎች አሁን በብሬንትፎርዱ አጥቂ ያአን ዊሳ ላይ ፍላጎት አሳይቶዋል።
ባለፈው የውድድር አመት የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ኤኬቲኬ እና ኦማር ማርሙሽ አስፈሪ ጥምረት የፈጠሩ ሲሆን ግን ማንቸስተር ሲቲ በጥር ወር ኦማር ማርሙሽን ሲያስፈርም ይህ ተበላሽቷል።
የኤኬቲኬ አጨዋወትን በተመለከተ እሱ ሁለገብ እና በሜዳው የሳጥን ውስጥ አጥቂ ብቻ ሳይሆን በጣም ተለዋዋጭ ተጫዋችም ነው ። ከማርሙሽ ጋር ሲጫወት ሁለቱም ቦታዎችን ያለማቋረጥ ይለዋወጡ ነበር።
ጋዲሳ መገርሳ
ሐምሌ 10ቀን 2017 ዓ.ም
