ከ 4 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት አስታወቀ

4.1 ሚሊየን የሚሆኑ ከድህነት ወለል በታች ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አገልግሎቱ አስታዉቋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት ከ13.67 ሚሊየን በላይ አባወራ እና እማወራዎችን አባል በማድረግ 4.1 ሚሊየን የሚሆኑ ከድህነት ወለል በታች ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ያምሮት አንዱአለም አስታዉቀዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ይሄን ያስታወቁት የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎትየ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም እና የ2018 አ.ም ዕቅድ እና ትውዉቅ የዉይይት መድረክ በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ባለበት መድረክ ላይ ነዉ፡፡

በአማካይ ከ63 ሚሊየን በላይ የሃገሪቷን ዜጎች የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም አስታዉቀዋል፡፡

ከከፋይ አባላት ከ11.9 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ አንስተዉ፤ ከተናጥል ድጎማ ከ3.3 ቢሊየን ብር በላይ መገኘቱን አስታዉሰዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከ15.2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *