በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከኦገስት 1 እስከ 10/2025 ወይንም ከሃምሌ 25 እሰከ ነሃሴ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጠንከር ያለ ዝናብ እንደሚኖር ገልጿል።
በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን መካከለኛው እና የሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ነጎድጓዳማ እና ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖርም አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም በደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
ልኡል ወልዴ
ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም
