ከሰሜን ዳርፉር ግዛት ወደ ሰሜናዊ ግዛት አድ ዲባ ሲጓዙ የነበሩ 17 ሱዳናውያን ተፈናቃዮች በረሀ ውስጥ ህይወታቸዉ ማለፉን የሰሜን ሱዳን ሰብዓዊ እርዳታ ኮሚሽን አስታወቀ።
የሰብአዊ እርዳታ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ አብዱራህማን አሊ፤ 10 ሴቶች እና 13 ሕፃናትን ጨምሮ በሕይወት የተረፉትን ወደ ሆስፒታል የማዘዋወር ስራ እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
በሕይወት ያሉት ሰዎች ያሉበት የስነ -ልቦና ሁኔታ አስቸጋሪ ነዉ ሲሉ ገልፀው፤ ድጋፍና ልዩ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በተደጋጋሚ በሚደርሱ ጥቃቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ወደ ሰሜን እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሲል ኮሚሽኑ መግለጹን የዘገበው ሚድል ኢስት ሞኒተር ነው።
ሀሚድ አብደላ
ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም
