76 ቢሊየን ብሩ ያልተጣራ መሆኑም ተገልጿል።
ኩባንያው በ2017 በጀት አመት በዕቅድ አስቀመጥኩት ካለው 1መቶ63 ቢሊየን ብር ውስጥ 1መቶ62 ቢሊየኑን ገቢ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል።
በውጭ ምንዛሪ ደግሞ ከ2መቶ13 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማድረጉንም ገልጿል።
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በተለያዩ ምክንያቶች አስቸጋሪ ዓመት ብናሳልፍም ከዕቅዳችን 99 በመቶውን ማሳካት ችለናል ብለዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ሊድ የተሰኘ የ3 አመት የዕድገት ስትራቴጂ በመስከረም ወር 2015 ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ይህ የሶስት ዓመት የዕድገት ስትራቴጂ ሲጀመር ተቋሙ ያገኘው ገቢ 61.3 ቢሊየን ብር እንደነበርም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስታውሰዋል።
በዛው ዓመት ከውጭ ምንዛሪ የተገኘው ገቢ ከ146 ሚሊየን ዶላር በላይ ነበር ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፤ አሁን የተገኘው ገቢ ከ2መቶ13 ቢሊየን ዶላር በላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የደንበኞች ቁጥርም 83.2 ሚሊየን መድረሱን አስታውቀዋል።
እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም
