ወደ ማዶ ትያትር ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል የገቢ ማሰባሰቢያ እንደሚያካሂድ አስታወቀ

ትያትሩ በሚታይባቸው ሀገራትና መድረኮች ከትያትሩ ጎን ለጎን ይህንን በጎ አላማ ለማሳካት ከማዕከሉ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል ነዉ የተባለዉ፡፡

በኢትዮጵያ የትያትር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ30 የዓለም ሀገራት መድረኮች የሚታይ ‹‹ወደ ማዶ›› ትያትር ዓለም አቀፍ የትያትር ጉዞ ሊጀመር መሆኑ ታዉቋል።

አንጋፋ ተዋንያን የሚተውኑበት ይህ ‹‹ወደ ማዶ›› የተሰኘው ትያትር በውጭ ሃገር መድረክ እንደሚመረቅም ተገልጿል፡፡

በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ተደርሶ በሴም አማኑኤል የተዘጋጀውን ይህን ትያትር ፕሮዲውስ ያደረገው ዋካ ፕሮሞሽንና ኤቨንት ነዉ፡፡

ትያትሩ የኮሜዲ ዘውግ ያለው ሲሆን፤ ለመስራት ብዙ አመታትን የፈጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ማህበራዊ ጉዳዮችን እያነሳ የሚሄድ በሕይወታችን ከሚገጥሙን ችግሮች ለመዉጣት የሚደረግን ትንቅንቅ የሚያሳይ ነው፡፡

‹‹ወደ ማዶ›› ዓለም አቀፍ የትያትር ጉዞ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ አህጉራት በሚገኙ ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ከ30 በላይ መድረኮች ላይ ይታያል ተብሏል፡፡

የትያትሩ ይፋዊ የመክፈቻ መርሃ ግብር በነሐሴ ወር በአፍሪካ የተለያዩ ሃገራት ይደረጋል ተብሏል፡፡

በትያትሩ ሃረገወይን አሰፋን ጨምሮ ሸዋፈራው ደሳለኝ እና የኋላእሸት ዘሪሁን ይተዉኑበታል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *