የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ በመጪው መስከረም ወር ይካሄዳል ተባለ።
የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ እና የተቀናጀ የቤተሰብ ፍጆታ ጥናት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ2016 እስከ 2018 ለማድረግ መታቀዱን አስታውቋል ።
ከነዚህ ቆጠራዎቾ ደግሞ አንዱ የኢኮኖሚ ድርጅቶቾ ቆጠራ ሲሆን በመሰከረም 2018 ዓም ይጀመራል ተብሏል፡፡
የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊና የመረጃ ስርጭት ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሲናገሩ ይህ ቆጠራ ከሌሎቹ ቆጠራ ለየት ባለመልኩ ብዙ ጥናት እና ጊዜ ይወስዳል ያሉ ሲሆን፣ የእነዚህ የኢኮኖሚ ድርጅቶች መቆጠር ለኢንዱስትሪም ይሁን ለገንዘብ ሚኒስቴር ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡
የመጀመሪያው የሆነው በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ከትልልቅ ድርጅቶች መንገድ ላይ እስካሉ ትንንሽ የኢኮኖሚ ተቋማት እንደሚካተቱ ያነሱት ሃላፊው፣ ከኢንዱስትሪ ሚኒስትር ጋር በጋራ እንደሚሰራ እና ለኢንዱስትሪ ፖሊሲ ቀረፃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል ሲሉ ሃላፊው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ለዓለም አሰፋ
ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም
