የአለም ጤና ድርጅት በጋዛ በሚገኙ የሰብዓዊ እርዳታ መስጫ ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን አወገዘ

በጋዛ በሚገኙ ተቋማት እና ሰራተኞቹ ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ተቀባይነት የሌለው ነው ብሎታል።

በድር አል ባላህ የሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች መኖሪያ ቤት ሦስት ጊዜ ጥቃት እንደደረሰበትም ተገልጿል፡፡

እየተካሄደ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት እሳት እየተነሳ እንደሆነ በመግለፅ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ የተደናገጡ ሠራተኞች በእግራቸው እንዲሸሹም አስገድዷቸዋል ነዉ የተባለዉ።

ወንድ ሠራተኞች በካቴና ታስረው እየተወሰዱ እና በጠመንጃ ማስፈራርያ እየደረሰባቸው ሲሆን፤ ሁለት ሠራተኞች እና ዘመዶቻቸው እስካሁን መታሰራቸውን ገልፀዋል።

አንድ የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኛ አሁንም በእስር ላይ መሆኑም ተነግሯል ።

የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ቁሳቁሶችን ለማከማቸት እና ለማሰራጨት የሚጠቀምበት መጋዘን ላይ ዝርፊያ እና ጥቃት ደርሶበታል ተብሏል።

ጥቃቶቹ የጤና መሠረተ ልማቶችን የማውደም አካል ናቸው ሲል ድርጅቱ ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ 88 በመቶ የሚሆነው የጋዛ ክፍል ወታደራዊ ትዕዛዝ ውስጥ በመሆኑ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ እንደሌለ ገልጿል።

የዓለም ጤና ድርጅት የታሰረው ሠራተኛዉ በአስቸኳይ እንዲፈታ እና ለሰብዓዊ ሠራተኞች እና መሠረተ ልማቶች ጥበቃ እንዲደረግም ጠይቋል ።

የተኩስ አቁም አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ከረዥም ጊዜ በፊት መደረግ የነበረበት ጉዳይ እንደሆነም ድርጅቱ ገልጿል።

ኤርሚያስ ገረመዉ

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *