ፈረንሳይ ለፍልስጤም የሃገርነት እዉቅና እሰጣለሁ ማለቷን አሜሪካ ‹የግዴለሽነት ተግባር ነዉ› በማለት ስትኮንን ሳዉዲ አራቢያ ደግሞ ታሪካዊ ክስተት ይሆናል ስትል አሞገሰች፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለፍልስጤም በመስከረም ወር ላይ በኒዮርክ ከተማ በሚካሄደዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመታዊ መደበኛ ስብሰባ ላይ እዉቅና ሰጣለሁ ማለታቸዉን አሜሪካ ‹‹ግዴለሽነት ነዉ›› በማለት ኮነነች ፡፡

ስፔን እና ሳዉዲ አራቢያ በበኩላቸዉ ታሪካዊ ክስተት ይሆናል በማለት የፈረንሳይን ሃሳብ አድንቀዋል፡፡

ፈረንሳይ ለፍልስጤም የሃገርነት እዉቅና ከሰጠች ፤ከጂ 7 ወይንም ከቡድን ሰባት አባላት ሃገራት መካከል ቀዳሚዋ ሃገር ትሆናለች ተብሏል፡፡

የፍልስጤም ባለስልጣናት የፈረንሳይን ውሳኔ በደስታ እንደሚቀበሉት ሲገልጹ የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ውሳኔው “ሽብርተኝነትን የሚሸልም” ነው ብለውታል።

በአንጻሩ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የፈረንሳይን ውሳኔ “ሃላፊነት የጎደለው” ሲሉ ገልጸውታል።

ልኡል ወልዴ

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *