ሩሲያና ዩክሬን በኢስታንቡል ያደረጉት ሥስተኛ ዙር የሰላም ንግግር ሲጠናቀቅ፤ የጦር እስረኞች ልውውጥ ላይ ከስምምነት ቢደርሱም ተኩስ ማቆም ላይ ግን አልተስማሙም።
በድርድሩ ሩሲያ በፕሬዝዳንቱ ረዳት ቭላድሚር ሜዲንስኪ፤ ዩክሬን ደግሞ በብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ኃላፊ ሩስተም ኡሜሮቭ መሪነት ተወክለዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች እያንዳንዳቸው 1 ሺህ2መቶ የጦር እስረኞች ለመለዋወጥ ሲስማሙ፤ ሩሲያ ተጨማሪ 3ሺህ ህይወታቸዉ ያለፈ የዩክሬን ወታደሮች አስክሬንን ለመመለስ ቃል ገብታለች።
ዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ፣ፑቲን ፣ኤርዶጋን እና ትራምፕን ያሳተፈ ጉባኤ እስከ ነሐሴ ወር መጨረሻ ድረስ እንዲካሄድ ጠይቃለች፡፡
በሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን በማስቆም ጊዜያዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግም ሐሳብ አቅርባለች ።
ሁለቱም ወገኖች በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ መሻሻል መኖሩን ቢገነዘቡም፤ሙሉ በሙሉ ተኩስ በማቆም ላይ የሚደረገው ድርድር አሁንም እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን፤ አጥፊውን ጦርነት ለማስቆም ‹‹ውጤት ተኮር ድርድሮች›› እንዲደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሀሚድ አብደላ
ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም
