የቀድሞ የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ቾጉኤል ማይጋ የህዝብን ገንዘብ አለአግባብ መጠቀም ጋር በተያያዘ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገለፀ።

የማሊ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቾጉኤል ማይጋ፤በስልጣን ዘመናቸው የፈጸሙትን የገንዘብ ጥፋት በሚመለከት አዲስ የህግ ክትትል እየተደረገባቸው ነው።

የሀገሪቱ ኦዲተር ጄኔራል ጽህፈት ቤት በማይጋ አመራር ስር የመንግስት ገንዘብ ተዘርፏል የሚል ጥርጣሬን በመጥቀስ ሰነዶችን ለፍርድ ቤት አስረክቧል።

ምርመራው የተከፈተው በማይጋ የስልጣን ዘመን ከህዝባዊ ፕሮጀክት ምረቃ ጋር በተያያዙ አጠራጣሪ ወጪዎች ላይ እንዲሁም ምክንያታዊነት የጎደላቸው የሚባሉ ተልዕኮ ነክ ክፍያዎች ላይ ተመስርቶ ነው።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ደጋፊዎች አሁንም ተቃውሞ ላይ ሲሆኑ ፤ድርጊቱንም የፖለቲካ አላማ አለው ሲሉ ጠቁመዋል።

በተያያዘ ዜና ፤ ከሰሞኑም የቀድሞው የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዝደንት በአገር ክህደት ወንጀል መከሰሳቸዉ ይታወሳል፡፡

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የቀድሞ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ካቢላ ላይ የተመሠረተው የአገር ክህደት ወንጀል ክስ በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ በሚገኝ ወታደራዊ ፍርድ ቤት መታየት መጀመሩን ያሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ተዘግቧል፡፡

አገሪቱን የሚመሩት ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ፤ የቀድሞውን ፕሬዝደንት ከኤም 23 የአማጺ ቡድን ጀርባ በመሆን ድጋፍ ይሰጣሉ ሲሉ ይወነጅሏቸዋል ሲል የዘገበዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ።

ሀኒፍ ሀምዛ

ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *