ጋዛ ‘እውነተኛ ረሃብ’ እያጋጠማት ነው አሉ ትራምፕ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በጋዛ ረሃብ የለም ካሉ በኋላ ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ “እውነተኛ ረሃብ” አለ ብለዋል።

ኔታኒያሁ እስራኤል በጋዛ ረሃብን እያባባሰች ነው መባሉን “ድፍረት የተሞላበት ውሸት” ነው ካሉ በኋላ በጉዳዩ ላይ ይስማማሉ ወይ ተብለው የተጠየቁት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፤ “አላውቅም። . . .እነዚያ ሕፃናት በጣም የተራቡ ይመስላሉ። . . . ይህ እውነተኛ የረሃብ ጉዳይ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታይመር ጋር በስኮትላንድ በነበራቸው ንግግር “በዚያ ማንኛውም ሰው የሰራው ትልቅ ነገር የለም። ሙሉ አካባቢው የተበላሸ ነው። . . . ለእስራኤል ምንአልባት ነገሮችን በተለየ መንገድ መስራት እንዳለባቸው ነግሬያቸዋለሁ” ብለዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር እሁድ ዕለት እስራኤል በጋዛ ሆን ብላ ንፁሃን ሰዎችን እያስራበች ነው መባሉን መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል።

“እንዴት ያለ ድፍረት የተሞላበት ውሸት ነው። በጋዛ የማስራብ ፖሊሲ የለም። እናም በጋዛ ረሃብ የለም” ብለዋል።

የትራምፕ አስተያየት የተሰማው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ ረሃቡን ለመቀልበስ “በጣም ብዙ” ምግብ ያስፈልጋል ማለታቸውን ተከትሎ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *