በኢትዮጵያ በአመት ከ2ሺ 7መቶ በላይ ሰዎች በውሻ እብደት በሽታ ህይወታቸው ያልፈል ተባለ ።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በሀገራችን ከ2ሺ 7መቶ በላይ ሞት በውሻ እብደት በሽታ እንደሚከሰት አስታውቋል ።

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና እና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ባለሙያ የሆት አቶ ንጉሴ ባዬ ለጣቢያችን እንዳሉት ከ250-300ሺ ውሾች ቢኖሩም 70 በመቶ የሚሆኑት ግን ባለቤት የሌላቸው ናቸው።

በአዲስ አበባ በ2017 አ.ም 4ሺ 9መቶ 45 ሰዎች በእብድ ውሻ ተነክሰው ምልክት ከማሳየታቸው በፊት ህክምናውን ለማግኘት ወደ ህክምና ተቋም መምጣታቸውን ተናግረዋል።

ለህክምና ከመጡት መካከል 47 የሚሆኑ ሰዎች ህክምናውን በመፍራት የሸሹ ናቸው ብለዋል።

በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ለመምጣቱ እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ነገሮች መካከል ሰዎች በባህላዊ ህክምናዎች መተማመናቸው እንደሆነ ባለሙያው ጠቅሰዋል።

እንዲሁም ለውሻ እብደት በሽታ የሚሰጡ መድሀኒቶችን አብዛኛው ማህበረሰብ ገንዘቡን መሸፈን የሚችለው ባለመሆኑ ዘርፉ ላይ ትልቅ ችግር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሀገራችን የውሻ እብደት በሽታ የብዙ ሰዎችን ህይወት የሚቀጥፍ ነገር ግን ብዙ ትኩረት ያልተሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *